Sidama Construction Works Corporation

Sidama Construction Works Corporation The Corporation aspires to be one of the leading construction companies in the region and in the country as well.

SIdama Construction Works Corporation(SCWC)
*******************************************************************
Sidama Construction Works Corporation (SCWC) was established following the final decentralization process of the former Southern Nations, nationalities, and people’s regional states and the disintegration of the former South Water Works Construction Enterprise (SWWCE). The corporation wa

s established to meet the infrastructure demand of the region’s society in accordance with the power given in Article 57(6) of the Regional Constitution, to the Executive Council of Sidama National Regional State with Regulation No. 30/2022 on December 6, 2023. Since its establishment it has been entering into contract with the regional water mines and energy bureau to carry out irrigation and water supply projects and also Building construction of various sizes. The corporation shall have the following responsibilities:
• Construction of dams, irrigation, water works, hydropower,
sewerage network, water well drilling, rehabilitation, and pumping
tests
• Construction of roads, bridges, buildings, integrated drainage
development, flood protection, and river diversion for different
purposes.
• Manufacture, import, sell, distribute, and rent different materials
and tools necessary for the fulfillment of its objectives.
• Issue bonds, use deposits as security, sell them, and get involved
in the stock market.
• Engage in various investment and development activities by
obtaining authorization of the authority.
• Carry out electromechanical work.
• Provide engineering-related consulting services related to water
works, roads, and building construction.

27/08/2026
27/08/2026
የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር  አቶ ደስታ ሌዳሞ የሩፎ ዋኤኖ ሞዴል ትምህርት ቤት ግንባታ ጎበኙ።ርዕሰ መስተዳድሩ በዛሬው ዕለት በፌደራል መንግስት ድጋፍ  በአለታ ጩኮ ከተማ በኮርፖ...
27/08/2026

የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሩፎ ዋኤኖ ሞዴል ትምህርት ቤት ግንባታ ጎበኙ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዛሬው ዕለት በፌደራል መንግስት ድጋፍ በአለታ ጩኮ ከተማ በኮርፖሬሽናችን በመገንባት ላይ የሚገኘውን የሩፎ ዋኤኖ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤት ግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል። ጉብኝቱን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በተጨማሪ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር እና የክልሉ የትምህርት ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ በየነ በራሳ፣ የኮርፖሬሽናችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኤልያስ ቲሮ እንዲሁም የክልሉ፣ የዞንና የወረዳ እና ከተማ አመራሮች በጋራ አካሂደዋል።
ነሐሴ 21/2018ዓ.ም.
ሲኮሥኮ
በጥራት አንደራደርም!

25/08/2026
የሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የበላይ ሥራ አመራር ቦርድ የ2018 በጀት ዓመት ዓመታዊ ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ገምግሞ አፀደቀ፡፡****************...
12/08/2026

የሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የበላይ ሥራ አመራር ቦርድ የ2018 በጀት ዓመት ዓመታዊ ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ገምግሞ አፀደቀ፡፡
*****************************************************
የሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች የሥራ አመራር ቦርድ ዛሬ ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ የ2018 በጀት ዓመት ዓመታዊ ዕቅድ አፈጻጸም ገምግሞ ያፀደቀ ሲሆን የተቋሙ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድና ቀጣይ የአፈጻጸም አቅጣጫዎችም ላይ ተወያይቷል፡፡
የኮርፖሬሽኑን ዓመታዊ ሪፖርት እና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ያቀረቡት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኤልያስ ቲሮ ኮርፖሬሽኑ በ2018 በጀት ዓመት በመስኖ፣ በመጠጥ ዉሃ፣ በጉድጓድ ቁፋሮ እና በህንፃ ግንባታ ዘርፍ ከ4.5 ቢሊየን ብር በላይ የዉለታ ዋጋ ያላቸዉ 76 ፕሮጀክቶችን ይዞ ሲገነባ የቆየ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ 54 ፕሮጀክቶች በበጀት ዓመቱ የተገኙ አዲስ ፕሮጀክቶች መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡ በገለፃቸዉም በበጀት አመቱ 19 ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ መቻሉን እንዲሁም ከ26,000 በላይ ዜጎች በፕሮጀክቶች ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፍጠሩንም አንስተዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ የነዳጅ አቅርቦት ከፍተኛ እጥረትና የግንባታ ማቴሪያሎች ዋጋ መናር የግንባታ ስራዉን የተፈታተኑ ችግሮች መሆናቸዉንም አስረድተዋል፡፡
ሥራ አመራር ቦርዱ ሪፖርቱን ካደመጠ በኋላ የኮርፖሬሽኑ አፈጻጸም በየጊዜው እያደገ መምጣቱን ከቀረበው ሪፖርት መመልከቱን አስገንዝቧል። ኮርፖሬሽኑ በአቅም ግንባታ ዘርፍ በበጀት ዓመቱ 5 ተሸከርካሪዎችን መግዛት መቻሉና፣ ማህበራዊ ሃላፊነትን ከመወጣት አንጻር ሰፊ ሥራ መሰራቱን በጥንካሬ የሚገመገም መሆኑን እንዲሁም ኮርፖሬሽኑ እንደኮሪደር ልማትና መሶብ ባሉ ሀገራዊ የግንባታ ሥራዎች መሳተፍ መጀመሩ እንዲሁም ከፌደራል ተቋማት ጋር መስራት መቻሉ ጥሩ ጅምር መሆኑን አስገንዝቧል፡፡ ከተሰብሳቢ ሂሳብ ጋር በተያያዘም ሥራ አመራር ቦርዱ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ተቋሙን ለመደገፍ ተልዕኮ ተቀብሏል።
የተቋሙ ሥራ አመራር ቦርድ ሠብሳቢ የተከበሩ አቶ አሸናፊ ኤልያስ በበኩላቸዉ ኮርፖሬሽኑ በክልሉ ሠፊ ሥራ መስራቱንና ከልማት ጋር የተያያዙ ብዙ ችግሮችን መፍታቱን እንዲሁም በክልሉ በሚገነቡ የመሶብ እና ኮሪደር ልማት ሥራዎች ከፍተኛ እገዛ ማድረጉን በማንሳት ኮርፖሬሽኑ ፕሮጀከቶችን በዉል ጊዜ ዉስጥ አጠናቆ በማስረከብ ተወዳዳሪ ተቋም ሆኖ መዉጣት እንዳለበት ገልፀዋል፡፡ በአጠቃላይ ቦርዱ ኮርፖሬሽኑ እያሳየ ያለዉ የሥራ አፈፃፀም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን በማሳሰብ የቀረበዉን ሪፖርት በሙሉ ድምፅ አጽድቋል፡፡
በተመሳሳይ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በተመለከተም ቦርዱ የቀረበዉን ዕቅድ በዝርዝር በመመልከት ፕሮጀክቶችን ከገበያ በዉድድር ማግኘት እና ከክልል ዉጪ መስራት ላይ፣ ከተቋሙ ጋር የሚሄዱ ተቋሙን በግብአት ሊያግዙ የሚችሉ ተጨማሪ የገቢ ማግኛ ተቋማት ግንባታ እንዲሁም ወጪ ቅነሳ እና ተቋም ሪፎርም ሥራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ በማሳሰብ በሙሉ ድምጽ ወስኖ ተቀብሎታል።
#ሲኮስኮ
ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም.
ጥራት ላለው ግንባታ-ሲኮስኮ
Follow Us on:
www.facebook.com/sidamaconstruction
www.t.me/scw_corporation
www.tiktok.com/
www.youtube.com/

የሲዳማ ኮንሥትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የ2018 በጀት አመት አጠቃላይ ዕቅድ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት እቅድና ቀጣይ አቅጣጫዎች ግምገማ አካሄደ ፡፡የሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮር...
11/08/2026

የሲዳማ ኮንሥትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የ2018 በጀት አመት አጠቃላይ ዕቅድ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት እቅድና ቀጣይ አቅጣጫዎች ግምገማ አካሄደ ፡፡
የሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች የተቋሙን የ2018 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ገምግመዋል፡፡ በተቋሙ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተቋሙ ሠራተኞችና አመራሮች በተገኙበት በተካሄደው በዚሁ መድረክ ላይ የተቋሙ አመታዊ የአፈጻጸም ሪፖርት እንዲሁም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድና ቀጣይ የአፈጻጸም አቅጣጫዎች በኮርፖሬሽናችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በአቶ ኤልያስ ቲሮ ቀርቦ ሰፊ ዉይይት ተደርጓል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኮርፖሬሽኑ የአጭር ጊዜ እድሜ ያለው ተቋም ቢሆንም በግንባታው ዘርፍ እያስመዘገበ ያለው ለዉጥ የሚታይ መሆኑን ጠቅሰው የአቅም ግንባታ ሥራዎችና የተቋሙን ካፒታል ማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራባቸው መቆየቱን በቀጣይም የሚቀጥል መሆኑን በመግለፅ እየታየ ያለው ዉጤት የአመራሩና የሠራተኛው የጋራ ዉጤት በመሆኑ ለዚህም ሠራተኛው ሊመሰገን የሚገባው መሆኑን አንስተዋል፡፡ በተቋሙ የሚታየው ጠንካራ የስራ ባህልም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
ከፕሮጀክት ግንባታ ጋር በተያያዘ በዚህ በጀት አመት የነዳጅ እጥረት እና የግንባታ እቃዎች ዋጋ መናር ከፍተኛ ተግዳሮት የነበሩ ቢሆንም ኮርፖሬሽኑ ፕሮጀክቶችን ገንብቶ ለማጠናቀቅ ጥረት ማድረጉን አምና በተመሳሳይ ጊዜ ከነበረው አፈጻጸምም ጋር ሲታይ የተሻለ መሆኑ ተነስቷል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በግንባታ ዘርፍ እያበረከተ ካለው አስተዋፅኦ ጎን ለጎን ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን የጠቀሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ማህበራዊ ሃላፊትን ከመወጣት አንጻርም በበጎ ፈቃድ ሥራዎች በመሳተፍ በበጀት ዓመቱ ሰፊ ስራ መስራቱን ይህም ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም ከዉይይቱ ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከመድረክ ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን መድረኩ የቀጣይ ዓመት ዕቅዶችን በዉጤታማነትና ተነሳሽነት ለመተግበር በተቀመጡ ግቦችና የአፈጻጸም አቅጣጫዎች ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ዉይይቱ ተጠናቋል፡፡
#ሲኮስኮ
ነሐሴ 4/2018 ዓ.ም.
ጥራት ላለው ግንባታ-ሲኮስኮ
Follow Us on:
Sidama Construction Works Corporation
www.t.me/scw_corporation
www.tiktok.com/
www.youtube.com/

በሲዳማ ክልል ጎርቼ ወረዳ በኮርፖሬሽናችን በመገንባት ላይ የሚገኘዉ የጎርቼ ሆስፒታል (ቤዝመንት+ጂ+2) የህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት የ2ኛ ወለል ስላብ ሙሌት ዝግጅት ሥራ በመከናወን ላይ ይገኛል...
08/08/2026

በሲዳማ ክልል ጎርቼ ወረዳ በኮርፖሬሽናችን በመገንባት ላይ የሚገኘዉ የጎርቼ ሆስፒታል (ቤዝመንት+ጂ+2) የህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት የ2ኛ ወለል ስላብ ሙሌት ዝግጅት ሥራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ የፕሮጀክቱን ሥራ በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የፕሮጀክቱ ሃላፊ ኢ/ር መሀመድ አሊ የህንጻ ግንባታ ስራው ከመሬት በታች ወለል (Basement Floor Slab) አስከ መጀመሪያ ወለል ድረስ ያለው የስላብ ሙሌት ስራ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ በአሁን ሰዓት የ2ኛ ወለል የስላብ የኮንክሪት ሙሌት ለማከናወን የፎርም ዎርክ እና የሪኢንፎርስመንት ባር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈጻጸምም በአሁን ሰዓት 49.7% ላይ ይገኛል፡፡
#ሲኮስኮ
ነሐሴ 2/2018 ዓ.ም.
ጥራት ላለው ግንባታ-ሲኮስኮ
Follow Us on:
Sidama Construction Works Corporation
www.t.me/scw_corporation
www.tiktok.com/
www.youtube.com/

ኮርፖሬሽናችን በሲዳማ ክልል በሰሜናዊ ዞን በወንዶ ገነት ከተማ እየገነባቸው ከሚገኙ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው የወንዶ ገነት ከተማ አስተዳደር የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል ግ...
03/08/2026

ኮርፖሬሽናችን በሲዳማ ክልል በሰሜናዊ ዞን በወንዶ ገነት ከተማ እየገነባቸው ከሚገኙ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው የወንዶ ገነት ከተማ አስተዳደር የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡
የፕሮጀክቱ ሥራ ከዚህ ቀደም የነበረዉን ህንጻ ለመሶብ አገልግሎት አመቺ በሆነ መልኩ በአዲስ መልክ የመገንባት፣ የግቢ ማስዋብና ላንድስኬፒንግ ስራ፣ የከንቲባ ጽ/ቤት እና የመሶብ ህንጻ የአጥርና የመግቢያ በር ግንባታ ሥራዎችን አካቶ የያዘ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ በአሁን ሰዓት 99% ላይ የሚገኝ ሲሆን በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ይጠበቃል፡፡
#ሲኮስኮ
ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም.
ጥራት ላለው ግንባታ-ሲኮስኮ
Follow Us on:
www.facebook.com/sidamaconstruction
www.t.me/scw_corporation
www.tiktok.com/
www.youtube.com/

የወንዶ ገነት መሶብ ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት- በምስል
22/07/2026

የወንዶ ገነት መሶብ ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት- በምስል

11/07/2026

Address

Behind Addisu Gebeya, Around Street George Church
Tamizhagam

Opening Hours

Monday 8:30am - 5:30pm
Tuesday 8:30am - 5:30pm
Wednesday 2:30am - 11:30pm
Thursday 2:30am - 11:30pm
Friday 8:30am - 5:30pm
Saturday 8:30am - 12:30pm

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sidama Construction Works Corporation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share