Kitatin Designs

Kitatin Designs We design all types of buildings, landscapes, logos, interiors and train variety of software.

Durame Stadium Zuria Kale Hywot Church Renovation and Expansion Project
02/03/2025

Durame Stadium Zuria Kale Hywot Church Renovation and Expansion Project

This project is designed by Marchitechn Designs for free. It has offices on the basement floor and the ground floor is worship Hall.

እንዴት አላችሁ ወዳጆች!ዛሬ በተለይ ከምባትኛ ለምትሰሙ ሰዎች አንድ ቆንጆ ስጦታ ይዤላችሁ መጥቻለሁ። ሙሉ አልበሙ የተሰራው የዛሬ 14 ዓመት አካባቢ ሲሆን እያንዳንዱ መዝሙር የሚገርም መልዕክ...
13/01/2024

እንዴት አላችሁ ወዳጆች!
ዛሬ በተለይ ከምባትኛ ለምትሰሙ ሰዎች አንድ ቆንጆ ስጦታ ይዤላችሁ መጥቻለሁ። ሙሉ አልበሙ የተሰራው የዛሬ 14 ዓመት አካባቢ ሲሆን እያንዳንዱ መዝሙር የሚገርም መልዕክት ያለው ነው። ሙዚቃውን እና ቅንብሩን ደግሞ አቤኔዘር ታፈሰ ቆንጆ አርጎ ሰረቶታል። ሆኖም ግን መዝሙሩ እንደዛሬው ዓይነት የመረጃ መለዋወጫ አውታር ሰፊ ካለመሆኑ የተነሳ ይመስለኛል መዳረስ ባለበት ልኩ አልተዳረሰም። እኔ ደግሞ በመዝሙሩ ባለቤቶች ይሁንታ አንዷን መዝሙር ብቻ በራሴ ተነሳሽነት ቪድዮ ሰርቼላችኋለሁ። በ"Marchitechn designs" YouTube ቻናሌ ላይ በመግባት መመልከት ይቻላል።
ተባረኩ!

The motion graphics for this gospel song is done by Marchitechn designs !

አርማ(Logo) ማለት ምን ማለት ነው? አርማ ማለት አንድን ኩባንያ ወይም ድርጅት የሚወክል ምልክት ሲሆን ሰዎች የምርት ወይንም የአገልግሎት ስም እንዲያውቁ እና እንዲያስታውሱ የሚረዳ ምስላዊ...
03/12/2023

አርማ(Logo) ማለት ምን ማለት ነው?
አርማ ማለት አንድን ኩባንያ ወይም ድርጅት የሚወክል ምልክት ሲሆን ሰዎች የምርት ወይንም የአገልግሎት ስም እንዲያውቁ እና እንዲያስታውሱ የሚረዳ ምስላዊ መለያ ነው። ብዙውን ጊዜ የኩባንያውን ወይንም የድርጅቱን እሴቶች፣ ተልዕኮ ወይም ምርቶች የሚያስተላልፍ የጽሑፍ እና የምስል ጥምረት ነው።
የየትኛውም መንግስታዊ ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አርማ ለበርካታ ቁልፍ ተግባራት ይጠቅማል።
1. መለያ፡ ሰዎች አንድን ኩባንያ ከተወዳዳሪዎቹ ለይተው እንዲያውቁ የሚያደርግ እና የአንድ ምርት ቶሎ የሚታወስና የሚታይ አካል ነው።
2. መልዕክት ማስተላለፍ፡ በሚገባ የተነደፈ አርማ ቃላት ሳያስፈልገው የኩባንያውን እሴት፣ ተልዕኮ ወይም ምርት ማስተላለፍ ይችላል።
3. ተዓማኒነትን መጨመር፡ ሙያዊ እና በደንብ የተሰራ አርማ ህጋዊነትን እና ሙያዊነትን ሊያስተላልፍ ይችላል፣ ይህም ደንበኞች እና አጋሮች ላይ እምነትን ያሳድጋል።
4. ቶሎ መታወስ፡ የሚስብ እና የማይረሳ አርማ በሰዎች አእምሮ ውስጥ የመጣበቅ ዕድሉ ከፍተኛ ነው፣ ይህም የምርት ስም ወይንም የአገልግሎት አይነትን ከማስታወስ ባለፈ እውቅናን ይጨምራል።
በመሰረቱ አርማ ከቆንጆ ምስል በላይ ነው። የኩባንያውን ስብዕና ለመገንባት እና ከደንበኞች ጤናማ ግንኙነት ለመፍጠር ወሳኝ ሚና የሚጫወት ስልታዊ መሳሪያ ነው። አርማ ስለብራንድ ምንነት እና እሴቶች ብዙ የሚናገር ዝምተኛ እንደራሴ(አምባሳደር) ነው።

what does logo mean?
A symbol representing a company or organization. A logo is a visual identity that helps people recognize and remember a brand. It's often a combination of text and images that conveys the company's values, mission, or products.
A logo representing a company or organization serves several key purposes:
1. Identification: A logo is the most recognizable visual element of a brand. It helps people instantly identify a company and differentiate it from its competitors.

2. Communication: A well-designed logo can communicate a company's values, mission, or products without needing words.

3. Credibility and trust: A professional and well-crafted logo can convey legitimacy and professionalism, fostering trust in potential customers and partners

4. Memorability: A catchy and memorable logo is more likely to stick in people's minds, increasing brand recall and recognition. This is crucial for building a strong brand identity and staying top-of-mind for consumers.

In essence, a logo is more than just a pretty picture. It's a strategic tool that plays a vital role in shaping a company's image and connecting with its audience. It's a silent ambassador that speaks volumes about the brand's essence and values.

እባክዎን ከታች ባሉ ሊንኮች ወደ youtube በመግባት በ Marchitechn Designs በተለያዩ ጊዜያት የተሰሩ ሎጎዎችን ይመልከቱ።
Please go to youtube through the following links to watch more!

https://youtu.be/L5-GQvfhc7I
https://youtu.be/tFa4XP9jw3g
https://youtu.be/rzdFjoZDa3M

ለእርስዎስ ምን ይሰራልዎ!
26/11/2023

ለእርስዎስ ምን ይሰራልዎ!

26/11/2023

እንዴት አላችሁ!
Youtube ቻናልህን Subscribe ለማድረግ ስንሞክር Sign in እያለ ተቸገርን ያላችሁኝ ሁሉ Please ቀጥሎ በማሳያችሁ ቅደም ተከተል እንደገና ሞክሩት!
ይህ ችግር በብዛት የሚከሰተው Facebook ላይ ከተቀመጠላችሁ ሊንክ ቀጥታ ወደ Youtube ስትገቡ ስለሆነ ከዚያ ይልቅ
1. በቅድሚያ ስልክ ላይ Youtube app መክፈት
2. በመቀጠል Search የሚለውን button በመጫን Marchitechn designs ብሎ search ማድረግ
3. ከዚያም መጀመሪያ ላይ ከሚመጣላችሁ ቪዲዮ ስር Subscribe የሚል አብሮ ሲመጣ Subscribe በማድረግ ሙሉ ቪድዮዎችን እዚያው መመልከት ይቻላል።
 በቀጣይ ዙር Logo (አርማ) እና በ Landscape ዙሪያ ያለን ዝግጅት በ Facebook ፔጃችንና በ Youtube ቻናላችን ስለሚለቀቅ follow እና subscribe ማድረጉን አትርሱ!
መልካም ቆይታ!

በyoutube እና በfacebook ፔጃችን የምንለቃቸው መረጃዎች እየደረሷችሁ ነው ብለን ተስፋ እናደርጋለን!በነገራችን ላይ የትኛውንም የዲዛይን  ስራ ማዘዝ ሲፈልጉ ​09 27 19 08 02 ...
20/11/2023

በyoutube እና በfacebook ፔጃችን የምንለቃቸው መረጃዎች እየደረሷችሁ ነው ብለን ተስፋ እናደርጋለን!
በነገራችን ላይ የትኛውንም የዲዛይን ስራ ማዘዝ ሲፈልጉ ​09 27 19 08 02 ብለው ይደውሉ!

ግቢዎን ከማሳመር ጀምሮ እስከ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ሃላፊነት ወስደን እናስደስቶታለን!
እኛን በማማከር ሃብትና ንብረትዎን ከብክነት ይታደጉ!

ዛሬም አንድ ቀለል ያለች ግን ደግሞ በጣም የምትወዷትን ስራ ልጋብዛችሁ!
ማሳሰቢያ፦ ፔጃችንን follow እና የyoutube ቻናላችንን ደግሞ subscribe ማድረግ ለእርስዎ የ 2 ደቂቃ ስራ ሲሆን ለእኛ ግን የእድሜ ልክ ማበረታቻ ነው!
ምርጫዎ ስላደረጉን እናመሰግናለን!

This stage is designed by Marchitechn designs.

የተወደዳችሁ!በዚህኛው FB page እና በYoutube ቻናላችን ለሁሉም የሚሆኑ በጣም ጠቃሚ ነገሮችን ለመልቀቅ ዝግጅታችንን እየጨረስን ነው። የምንለቃቸው ነገሮች እንዳያመልጧችሁ fb ፔጃችንን...
18/11/2023

የተወደዳችሁ!
በዚህኛው FB page እና በYoutube ቻናላችን ለሁሉም የሚሆኑ በጣም ጠቃሚ ነገሮችን ለመልቀቅ ዝግጅታችንን እየጨረስን ነው። የምንለቃቸው ነገሮች እንዳያመልጧችሁ fb ፔጃችንን follow እና youtube ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ብትቀላቀሉን ታተርፉበታላችሁ!
ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን አንድ ቀለል ያለ ስራችንን በyoutube ቻናላችን ተመልከቱ!
መልካም ቀን!
https://youtu.be/PYeXdXnlxy4?si=ZEebIZv5BGWCja03

የተወደዳችሁ!ባለፈው ባጋረኋችሁ ጽሑፍ ከተማን የሚቀርጹ እና የሚገልጹ አንድ የከተማ ዲዛይን ሊያካትታቸው ስለሚገቡ መሰረታዊ ነገሮች አንስቼ ሳልቋጭ እንደተሰናበትኩ ታስታውሳላችሁ! ዛሬም ቢሆን...
16/11/2023

የተወደዳችሁ!
ባለፈው ባጋረኋችሁ ጽሑፍ ከተማን የሚቀርጹ እና የሚገልጹ አንድ የከተማ ዲዛይን ሊያካትታቸው ስለሚገቡ መሰረታዊ ነገሮች አንስቼ ሳልቋጭ እንደተሰናበትኩ ታስታውሳላችሁ! ዛሬም ቢሆን የማያልቅ ጉድ ስለሆነ የተወሰነውን ብቻ አነሳላችሁና እናንተ እንድታነቡ ፍንጭ ሰጥቼአችሁ እቋጫለሁ። መልካም ንባብ!

4. ተደራሽነት(Accessibility)
ተደራሽነት ሰዎች እንዴት በቀላሉ እና በተመቻቸ ሁኔታ በከተማ ዙሪያ መጓዝ እንደሚችሉ ያመለክታል። ይህም የተለያዩ የመጓጓዣ ዘዴዎችን ማለትም የህዝብ መጓጓዣ ለመጠቀም፣ የእግር ጉዞ ለማድረግ እና ብስክሌት ለመንዳት አመቺነትን እንዲሁም የአካል ጉዳተኞችን ለማስተናገድ የሚሆኑ መንገዶች ዲዛይንን ያጠቃልላል።

5. ዘላቂነት(sustainability)
ዘላቂነት በከተማ ዲዛይን ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ አስፈላጊ ትኩረት እየተሰጠው የመጣ ጉዳይ ነው። የኃይል ፍጆታ እና ብክለትን መቀነስ እንዲሁም አረንጓዴ ቦታዎችን ማጠናከርን ያጠቃልላል። ለምሳሌ አንድ የህንፃ ዲዛይን በራሱ የኃይል ቆጣቢ (energy efficient) በሆነ መንገድ ሲሰራ በአጠቃላይ ከተማው በአከባቢ ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ አዎንታዊ ይሆናል። አንድ ሕንጻ ኃይል ቆጣቢ የሚሆነው እንዴት ነው?(ሌላ ጊዜ በሰፊው እንመለስበታለን)። ዘላቂነት ያለው ከተማ አካባቢን ለመጠበቅ(Environmental) ፣ማህበራዊ ፍትህን(Social) ለመጠበቅ እና ማንንም ወደ ኋላ የማይተው ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚያዊ(Economical) ልማትን ለማስፈን የተገነባ የመኖሪያ ቦታ ነው።

6. ማንነት(Identity)
የአንድ ከተማ ማንነት እራሱን ከሌሎች ከተሞች የሚለይ ልዩ ባህሪ ነው። ይህንን በቀላሉ ለመረዳት አጠገባችሁ ያለው ሰው ከእናንተ የሚለይባቸውን ባህሪያት ማስታወስ ነው።ማንነት የከተማዋን ታሪክ፣ ባህል እና አርክቴክቸርን ጨምሮ በተለያዩ ሁኔታዎች የተቀረፀ ነው። ከተማችን ቁርጥ እንትና የሚባለውን ከተማ ይምሰልልኝ ከሚለው ሃሳብ መላቀቅ ስንችል ከሌሎች ከተሞች በቀላሉ ሊለየው የሚችል የሆነ የራሱ የሆነ ማንነት እንዲነበብበት አርገን መገንባት እንችላለን።

ስለከተማ ዲዛይን በደንብ መረዳት ውስጣችን ከሆነ ደግሞ ቀጥሎ ያሉትን ለከተማ ዲዛይን አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች መካከል የሚጠቀሱትን የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ለማንበብና ለመረዳት እንሞክር። (Edges, Districts, Landmarks, Paths and Nodes)

እኔ ምለው! ከታች በምስሉ ላይ የምመለከቷቸው ስዎች እርስዎ በሚኖሩባት ከተማ ላይ ደህና ናችው? መውጣት መግባት እየቻሉ ነው? ወይስ ሳይወዱ በግድ የሚያመላልሳቸው ሰው ላይ ጥገኛ ሆነዋል? እስኪ ከላይ በ4ኛው ላይ ካነሳሁት ሃሳብ ጋር በማገናኘት በከተማዎ ላይ ስለነዚህ ሰዎች ደህንነት በኮሜንት ያሳውቁኝ። በጣም አሳስቦኛል!
ጨረስኩ

Address

Durame

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kitatin Designs posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share