ወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት Wollo Rural Road Maintenance Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Dessie
  • ወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት Wollo Rural Road Maintenance Office
Directions

ወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት Wollo Rural Road Maintenance Office Wollo Rural Road Maintenance Office

ለወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ፅ/ቤት ማኔጅመንት ደማቅ አቀባበል ተደረገየወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ፅ/ቤት የላቀ ውጤት በማስመዝገቡ የጥገና  ፅ/ቤቱ ሰራትኞች በኮመቦልቻ ኤርፖርት በመገኘት ደማቅ...
08/08/2026

ለወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ፅ/ቤት ማኔጅመንት ደማቅ አቀባበል ተደረገ

የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ፅ/ቤት የላቀ ውጤት በማስመዝገቡ የጥገና ፅ/ቤቱ ሰራትኞች በኮመቦልቻ ኤርፖርት በመገኘት ደማቅ አቀባበል አድርገዋል፡፡
በ2018 በጀት ዓመት የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የሚገኙ 6 /ስድስት/ መንገድ ጥ/ጽ/ቤቶች የአፈፃፀም ግምገማና ምዘና አካሄደ ።
ወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ፅ/ቤት በተካሄደው የምዘና መስፈርት መሠረት አብላጫ ውጤት በማስመዝገብ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀ በመሆኑ የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክቶለታል።
ይህ እውቅናና ሽልማት በተወሠኑ ሠዎች ጥረት የተገኘ ሣይሆን በሁሉም የጥገና ጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተናጠልም ሆነ በቡድን የሠሩት ድምር ውጤት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን በማለት የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መሀመድ ፈጠነ መልእክት አስተላልፈዋል።

ይህ የተሠጠን እውቅናና ሽልማት ከከፍተኛ አደራና ኃላፊነት ጋር አብሮ በመሆኑ በቀጣይ ዓመትም ከዚህ የበለጠ ውጤት እንዲመዘገብ በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅብናል በማለት ኃላፊው አክለው ገልፀዋል።
አስተያየታቸውን የሠጡ ባለሙያዎችም ሽልማቱ የሚያበረታታና ከዚህ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በትጋት እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል።

የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን ከጠቅላላ ሰራተኞች ጋር ገመገመ  ጥገና ጽ/ቤቱ በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ በየሂደቱ ሪፖርት ቀርቦ ...
02/08/2026

የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን ከጠቅላላ ሰራተኞች ጋር ገመገመ

ጥገና ጽ/ቤቱ በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ በየሂደቱ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡ተቋሙ በበጀት ዓመቱ በየዘርፉ የተለያዩ ተግባራትን አቅዶ ለመፈፀም ጥረት ያደረገ ሲሆን የተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን ተግባራት በአድሱ በጀት ዓመትም አጠናክሮ ለማቀጠል፣ በአፈጻጸም ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች ከየሂደቱ ተነስተው ሰፊ ውይይት እና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን ባለሙያዎችንና ሂደት የዕውቅ እና ሽልማት መርሃ -ግብርም ተከናውኗል፡፡ አስተያየት የሰጡ ባለሙያዎችም በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ መሟላት የሚገባቸውን ግብዓቶች በማንሳት እና የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ቃል በመግባት የግምገማ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

እንደ ሀገር አቀፍ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪቃል በክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብርን በማስመልከት የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ሠራተኞች በ25/11/2018 ዓ.ም በተቋሙ ቅጥር...
02/08/2026

እንደ ሀገር አቀፍ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪቃል በክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብርን በማስመልከት የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ሠራተኞች በ25/11/2018 ዓ.ም በተቋሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሄዱ፡፡ በዚህ ክረምት ለግቢ ውበትና አረንጓዴ ልማት አገልግሎት የሚውሉ 500 የፈረንጅ ፅድ 500 ግራቪሊያ እና 500 ቦትልብርቭ ችግኞችን የተቋሙ ሁሉም ሠራተኞች በተገኙበት አሻራቸውን አስቀምጠዋል፡፡ ችግኝ መትከል ከውበት አልፎ የአየር ንብረት መዛባትን የሚያስተካክል በመሆኑ መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብም እንደሚገባ ተግልጿል፡፡

19/02/2026

Address

Dessie
60

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት Wollo Rural Road Maintenance Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share