16/09/2026
ሰዎች በምን አይነት ከባድ የህይወት ፈተና ውስጥ እያለፉ እንደሆነ አታውቅም
| ተማሪዎች በምረቃ ቀናቸው መምህራኖቻቸውን ማመስገናቸው የተለመደ ነው።
በአሜሪካ ሮድ አይላንድ በተካሄደ አንድ የትምህርት ቤት የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ ምሩቁ ተማሪ ፊሊፕ ስፕራድሊን የምረቃ ቆቡንና ጋውኑን እንደለበሰ ከአራተኛ ክፍል ጀምሮ ሲመግበው ወደነበረውና በሁሉም ተማሪዎች ዘንድ ወደሚወደደው የምግብ አዳራሽ ሰራተኛ ዲኦን ሉካስ ዘንድ በመሄድ በስሜት ተሞልቶ እቅፍ አድርጓታል።
በቪዲዮ ተቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በተሰራጨው ቪዲዮ ላይ ተማሪው አጥብቆ ሲያቅፋትና ዲኦን ደግሞ አይኖቿን ጨፍና የደስታ እንባዎቿ በጉንጮቿ ላይ ሲፈሱ ያሳያል።
ዲኦን «ሰዎች በምን አይነት ከባድ የህይወት ፈተና ውስጥ እያለፉ እንደሆነ አታውቅም» በሚል የህይወት መመሪያ በመመራት፣ ከጠዋት እስከ ማታ በክፍል አዳራሹ ሙሉ ቀን በቆመችበት ፍቅሯን ለተማሪዎች ስትሰጥ የምትኖር ታታሪ ሰራተኛ ናት።
ለፊሊፕ ግን ዲኦን የምግብ ሰራተኛ ብቻ አልነበረችም፤ ከትምህርት ቤት ጫና፣ ከውጤት ስጋትና ከሰዎች ፍርድ ነጻ የሆነ ሰላምና ያልተገደበ እውነተኛ ፍቅር የሚያገኝበት መጠጊያው ነበረች።
በየቀኑ የምናሳያቸው ትናንሽ የደግነትና የርህራሄ ተግባራት የሰዎችን ህይወት ለዘላለም የመቀየርና የመቅረጽ ትልቅ አቅም እንዳላቸው ማሳያ ነው።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)