Ethiopian Electric Power-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

Ethiopian Electric Power-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል Ethiopian Electric Power is a state-owned electric producer in the Federal Democratic Republic of Ethiopia Telephone:- 011-5-580-631

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ......///.......በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በጀንደርና ሶሻል አፌይርስ ኦፊሰር - 5ኛ (Gender and Social Affairs Expert V) የሥራ መደብ ...
29/05/2026

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ......///.......
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በጀንደርና ሶሻል አፌይርስ ኦፊሰር - 5ኛ (Gender and Social Affairs Expert V) የሥራ መደብ ላይ አወዳድሮ ለመቅጠር የካቲት 05 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የውጭ ማስታወቂያ መውጣቱ ይታወሳል፡፡

በመሆኑም የቀረበውን መስፈርት አሟልታችሁ የጽሁፍ ፈተና ከወሰዳችሁ መካከል ስም ዝርዝራችሁ ከዚህ በታች የተገለጸው አመልካቾች፤ ዕሮብ ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ጠዋት 2፡30 ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ኮተቤ በሚገኘው የተቋሙ ዋና መ/ቤት ለሚሰጠው የቃል ፈተና እንድትገኙ እናሳስባለን።

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/
📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/
📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et
ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም

 1፡ ታሪካዊ ስኬት ለሀገራችን!ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP 32) ለማስተናገድ መመረጧ፣ በታዳሽ ኃይል ልማትና በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የደረሰችበትን የ...
29/05/2026


1፡ ታሪካዊ ስኬት ለሀገራችን!

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP 32) ለማስተናገድ መመረጧ፣ በታዳሽ ኃይል ልማትና በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የደረሰችበትን የላቀ ደረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከውሃ፣ ከንፋስ፣ ከፀሐይና ከእንፋሎት (Geothermal) 100% ንፁህና ለአየር ንብረት የማይበክሉ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን በስፋት በመገንባት የሀገራችንን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ በግንባር ቀደምትነት እየመራ ይገኛል።

ኮፕ 32 ተቋማችን የሚያመነጨውን ዘላቂ ኃይል ለዓለም አቀፍ ባለሀብቶችና ለአጋር ድርጅቶች ለማስተዋወቅ ትልቅ ድልድይ ነው!

ኃይል ለኢትዮጵያ ብልጽግና፣ ንፁህ ኢነርጂ ለዓለም ደህንነት!



💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/
📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/
📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et
ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም

የእስልምና እምነት ተከታይ ለሆናችሁ የተቋማችን አመራሮችና ሰራተኞች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!የአረፋ በዓል የታላቅ መስዋዕትነት፣ የጽናት...
27/05/2026

የእስልምና እምነት ተከታይ ለሆናችሁ የተቋማችን አመራሮችና ሰራተኞች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የአረፋ በዓል የታላቅ መስዋዕትነት፣ የጽናት፣ የሰዋዊ መተሳሰብና ለላቀ ዓላማ የመገዛት ታላቅ ተምሳሌት ነው።

ተቋማችን በሀገሪቱን እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት አስተማማኝና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨትና በማስተላለፍ ረገድ ሀገራዊ ኃላፊነት በቁርጠኝነት እየተወጣ ይገኛል።

ይህን ትልቅ ሀገራዊ ተልዕኮ ይበልጥ ወደ ላቀ ስኬት ለማሸጋገርእንደ በዓሉ እሴቶች ሁሉ የሁላችንም የጸና ቁርጠኝነት፣ የጋራ ትብብርና ሙያዊ መስዋዕትነት እጅግ አስፈላጊ ነው።

ሀገራችንን የብርሐን ማማ ላይ ለማድረስ ቀን ከሌሊት ለምትተጉ መላው የተቋማችን አመራሮችና ሠራተኞች ለምታበረክቱት ተቋማዊና ሀገራዊ ውለታ ተቋሙ ታላቅ ክብርና እውቅና ይሰጣል።

የዘንድሮው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ለሀገራችን ሰላምና አንድነትን ለተቋማችን አዳዲስ ስኬቶችን ለሁላችንም ደግሞ የስራ ተነሳሽነታችንን የሚያድስ እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ።

ዒድ ሙባረክ!

ኢ/ር አሸብር ባልቻ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/
📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/
ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም

የውጤት ማሳወቂያ ......///......የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሞግዚት/Child Caregivers /የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር በቁጥር ኢ.ኤ.ኃ/8.4/169/18 የካቲ...
26/05/2026

የውጤት ማሳወቂያ
......///......
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሞግዚት/Child Caregivers /የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር በቁጥር ኢ.ኤ.ኃ/8.4/169/18 የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም የውጪ ማስታወቂያ አውጥቶ ሚያዚያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም የፅሁፍ የተግባር ፈተና መሰጠቱ ይታወቃል፡፡

ስሆነም መስፈርቱን አሟልታችሁ ከተመዘገባችሁ ተወዳዳሪዎች መካከል የስም ዝርዝራችሁ ከተራ.ቁ1 እስከ 5 የተገለጸው አመልካቾች ከግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5/አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሰው ኃይል ቅጥርና ምደባ ቢሮ የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውን እና ኮፒ በመያዝ እየቀረባችሁ የቅጥር ፎርም እንድትሞሉ እናሳውቃለን፡፡

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/
📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/
📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et
ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም

የኃይል ማመንጫ ግድቦች በጥሩ የደህንነት ቁመና ላይ ይገኛሉየኃይል ማመንጫ ግድቦች በአስተማማኝ እና በጥሩ የደህንነት ቁመና ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።በተቋሙ ጀኔሬ...
26/05/2026

የኃይል ማመንጫ ግድቦች በጥሩ የደህንነት ቁመና ላይ ይገኛሉ

የኃይል ማመንጫ ግድቦች በአስተማማኝ እና በጥሩ የደህንነት ቁመና ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

በተቋሙ ጀኔሬሽን ቢዝነስ የግድብ ደህንነት ክትትል እና ቁጥጥር ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤሊያስ ደላሽ እንዳስታወቁት የግድቦችን ደህንነት ለማረጋገጥና ሊከሰቱ ለሚችሉ ችግሮች አስቀድሞ የመፍትሔ እርምጃዎችን ለመውሰድ በግድቦችና ተያዥ አካላት ላይ በየጊዜው የክትትልና ቁጥጥር ሥራ ይከናወናል፡፡

በዚህም ባለፉት አስር ወራት በመበልካ ዋከና፣ በግልገል ጊቤ አንድና ሁለት፣ ጊቤ ሶስት፣ ጢስ አባይ፣ ጣና በለስ፣ ቆቃ፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ ገናሌ ዳዋ፣ ተከዜ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች እና በኮይሻ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ፕሮጀክት ግድብ እና ተያያዥ ህዳጎች ላይ የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎች መከናወናቸውን ገልፀዋል፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ…
https://www.eep.com.et/?amh-news=የኃይል-ማመንጫ-ግድቦች-በጥሩ-የደህንነት&lang=am

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/
📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/
📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et
ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም

የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው የግንባታ አፈፃፀም ከ96 በመቶ በላይ ደርሷል..///....ለገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ኤሌክትሪክ ለማቅረብ እየተገነባ የሚገኘው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ...
23/05/2026

የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው የግንባታ አፈፃፀም ከ96 በመቶ በላይ ደርሷል..///....
ለገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ኤሌክትሪክ ለማቅረብ እየተገነባ የሚገኘው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ አጠቃላይ ግንባታ 96 ነጥብ 5 በመቶ መድረሱን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት 1 ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ።

በተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ የተመራ ከፍተኛ የሥራ አመራር ቡድን ለገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ እየተገነባ የሚገኘውን ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት ያለበትን የግንባታ ደረጃ በመስክ በመገኘት ገምግሟል።

የመስክ ግምገማው ፕሮጀክቱ የደረሰበትን የመጨረሻ ምዕራፍ የግንባታ አፈፃፀም እና በግንባታ ሂደቱ ላይ እያጋጠሙ የሚገኙ የዕቃ አቅርቦት ተግዳሮቶች ዙሪያ ተወያይቶ መፍትሄ ለመስጠት ያለመ ነው።

በዚሁ የመስክ ጉብኝት ወቅት ለከፍተኛ የሥራ አመራር ቡድኑ ገለፃ ያደረጉት በኢንጅነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት 1 ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ ተሾመ እንደተናገሩት በማከፋፈያ ጣቢያው ውስጥ እየተከናወኑ የሚገኙ የፍተሻና የማስተካከያ ሥራዎች የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል።

የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ከሚኖሩት አራት ባለ 63 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመሮች መካከል 50 ሜጋ ዋት ኃይል የመጫን አቅም ያለው አንዱ ትራንስፎርመር በተንቀሳቃሽ ስዊችጊር አማካኝነት አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።

በማከፋፈያ ጣቢያው ውጫዊ ክፍል የተተከሉ መሣሪያዎችን የመፈተሽ ሥራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን በመጥቀስ ሁለተኛውን የፍተሻ ሥራ ለማከናወን የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

አንዳንድ የመቆጣጠሪያ ኬብሎች እና የኮሙዩኒኬሽን መሣሪያዎች በዕቃ አቅራቢ ኩባንያው በኩል ባለመቅረባቸው የተነሳ የሥራ መዘግየቶች እያጋጠሙ መሆኑንም ነው ያብራሩት።

በአሁኑ ወቅትም የመቆጣጠሪያ ኬብሎችን እጥረት ለመቅረፍ ከሌሎች የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች በውሰት የማምጣት ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም አስረድተዋል።

የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አማካሪ አቶ ደመላሽ ሙሉ እንደገለፁት በኢኮኖሚ ዞኑ ውስጥ የሚገኙ ፋብሪካዎች በፍጥነት ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ ፕሮጀክቱን በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ማጠናቀቅ ይገባል።

በማከፋፈያ ጣቢያው ያለውን ከፍተኛ የውሃ አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከውሃ ምንጩ እስከ ጣቢያው ድረስ የ3 ኪሎ ሜትር የውሃ ቧንቧ መስመር ለመዘርጋት ዕቅድ መያዙን ተናግረዋል።

ዕቃ አቅራቢ ኩባንያው የቀሩትን ዕቃዎች በአስቸኳይ እንዲያቀርብና የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር የተቋሙ የሥራ አመራር ቡድን ጥብቅ መመሪያም አስተላልፏል።

የኃይል ማከፋፈያው የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ባለስልጣን ለሚፈልገው አገልግሎት ኃይል የሚያቀርቡ 14 ባለ 33 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች እንዲኖሩት ተደርጎ እየተገነባ የሚገኝ ጣቢያ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ የግንባታ እና የማማከር ሥራ በተቋሙ የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ዘርፍ በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን ለግንባታ ሥራው የሚያስፈልገው ወጪም በገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ባለስልጣን እየተሸፈነ ይገኛል፡፡

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/
📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/
📌ድረ- ገፅ https://www.eep.com.et
ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም

ፕሮጀክቱን በተያዘለት የጊዜ ገደብ አጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ ጥረት ይደረጋል‎…....///.......‎ የገንደ አርባ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታን በተያ...
23/05/2026

ፕሮጀክቱን በተያዘለት የጊዜ ገደብ አጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ ጥረት ይደረጋል
‎…....///.......
‎ የገንደ አርባ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታን በተያዘለት የጊዜ ገደብ አጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ ጥረት እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

‎በተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ የተመራ ከፍተኛ የሥራ አመራር ቡድን ለቡልቡላ የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ እየተገነባ የሚገኘውን የገንዳርባ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት ያለበትን የግንባታ ደረጃ በመስክ በመገኘት ገምግሟል።

የመስክ ግምገማው ፕሮጀክቱ የደረሰበትን የግንባታ አፈፃፀም እና በግንባታ ሂደቱ ላይ በሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ ተወያይቶ መፍትሄ ለመስጠት ያለመ ነው።

‎በመስክ ግምገማው ወቅት በተቋሙ የኢንጅነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ውድነህ የማነ እንደገለፁት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እና ወጪ የማይጠናቀቁት በወቅቱ የክትትልና ድጋፍ ሥራዎች በትኩረት ስለማይሰሩ ነው።

ፕሮጀክቱ በአሁኑ ወቅት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የገለፁት ኢንጂነር ውድነህ ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች አቅርቦት ችግሮች በመፈታታቸው ዕቃዎቹ በአሁኑ ወቅት ወደ ጣቢያው እየገቡ መሆኑን አብራርተዋል።

ከዚህ በኋላ ተከታታይ የሆነ የዕቃዎች አቅርቦት የሚኖር ከሆነ ፕሮጀክቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግ እንደሚቻል አረጋግጠዋል።

በአሁኑ ወቅት በፕሮጀክቱ የግንባታ ሂደት ላይ ማነቆ ሆኖ እየተስተዋለ ያለውን የነዳጅ አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ ከአካባቢው መስተዳድር አካላት ጋር በቅርበት በመተባበር መፍትሔ ለመስጠት እንደሚሰራም አስታውቀዋል።

ፕሮጀክቶችን በታቀደላቸው የጊዜ ገደብና ወጪ ለማጠናቀቅ ከተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጀምሮ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች በሪፖርት ብቻ ሳይወሰኑ በመስክ ተገኝተው መገምገማቸው ለሥራው መፋጠን ከፍተኛ መነቃቃትን እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

‎እንደ ኢንጂነር ውድነህ ገለፃ በየጊዜው በሥራ መሪዎች የሚደረጉ የመስክ ምልከታዎች በፕሮጀክት ግንባታዎች ላይ ለሚስተዋሉ ችግሮች አፋጣኝ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ ይረዳል።

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/
📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/
📌ድረ- ገፅ https://www.eep.com.et
ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም

በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ደርሶበት የነበረው መስመር ተጠግኖ ኃይል መስጠት ጀምሯል...…///…....ከባድ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የመልካ ዋከና - ራይቱ - ጎዴ ባ...
22/05/2026

በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ደርሶበት የነበረው መስመር ተጠግኖ ኃይል መስጠት ጀምሯል...…///…....
ከባድ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የመልካ ዋከና - ራይቱ - ጎዴ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር በጊዜያዊነት ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ 1 ሪጅን አስታወቀ።

የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ንጉሴ እንደገለጹት ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ባሌ ዞን ጊኒር ወረዳ "ኦዳ" በተባለ ልዩ ቦታ ላይ ከባድ ንፋስ ንፋስ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ በመስመሩ ላይ ስድስት የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎችን እንዲወድቁ አድርጎ ነበር።

በዚህ የተነሳ ከመስመሩ ኃይል ሲያገኙ የነበሩት የጎዴ እና የቀብሪደሃር ማከፋፈያ ጣቢያዎች እና ከጣቢያዎቹ ኃይል ሲያገኙ በነበሩ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ኃይል ተቋርጦ መቆየቱን አስታውሰዋል።

የወደቁትን ስድስት ከፍተኛ የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ሙሉ በሙሉ ጠግኖ ወደ መደበኛ አገልግሎት ለማስገባት ረጅም ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም የኅብረተሰቡን እንግልት ለመቀነስ እና ለአካባቢው አስቸኳይ ኃይል ለመስጠት ጊዜያዊ የአማራጭ ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውንም ገልጸዋል፡፡

በዚህም አምስት ባለ 132 ኪሎ ቮልት እና አንድ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎችን በመጠቀም ኃይል የተቋረጠባቸው አካባቢዎች በጊዜያዊነት መልሰው ኃይል እንዲያገኙ መደረጉን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

የወደቁትን ታወሮችን በዘላቂነት ለመጠገን የሚደረገው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በአካባቢው የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ወደነበረበት እስከሚመለስ ድረስ በትዕግስት ለጠበቁ ደንበኞች እና ለሥራው እገዛ ላደረጉ አካላት ዳይሬክተሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡።

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/
📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/
📌ድረ- ገፅ https://www.eep.com.et
ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም

የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው መገንባት ለስልጤ ዞን ሁለንተናዊ ዕድገት አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል..///... የወራቤ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ መገንባት ለስልጤ ዞን ሁለንተናዊ ...
22/05/2026

የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው መገንባት ለስልጤ ዞን ሁለንተናዊ ዕድገት አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል..///...
የወራቤ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ መገንባት ለስልጤ ዞን ሁለንተናዊ ዕድገት አዲስ ምዕራፍ መክፈቱን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ገለፁ።

ዋና አስተዳዳሪው አቶ ዘይኔ ቢልካ በጣቢያው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር የኃይል መሠረተ ልማቱ ተጠናቆ ለአገልግሎት መብቃቱ ለአካባቢው የኢኮኖሚ፣ የኢንዱስትሪና የማህበራዊ ልማት መፋጠን የጎላ ድርሻ ይኖረዋል።

ዞኑ ሰፊ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚካሄድበት ከ1 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ያረፈ የኢንዱስትሪ መንደር ልማት የተጀመረበትና ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፍላጎት ያለበት አካባቢ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ይሁን እንጂ ባለፉት ዓመታት ያጋጥም የነበረው የኃይል አቅርቦት እጥረት ችግር የአካባቢውን እምቅ የኢኮኖሚ አቅም ለመጠቀም ትልቅ ማነቆ ሆኖ መቆየቱን አስታውሰዋል።

የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት መብቃቱ ችግሩን በዘላቂነት ከመፍታቱም በላይ ለተጀመሩት የልማት ሥራዎችና ለአዳዲስ ኢንቨስትመንቶች አስተማማኝ ግብዓት መሆኑን አስገንዝበዋል።

የወራቤ ከተማ በርካታ መጋቢ መንገዶችና የንግድ መስመሮች የሚገናኙባት ስልታዊ ቦታ መሆኗን የጠቆሙት ዋና አስተዳዳሪው አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል መገኘቱ የከተማዋንና የአካባቢውን የንግድ ትስስር ይበልጥ እንደሚያሳድገውም ነው የገለፁት።

እንደ አቶ ዘይኔ ገለፃ በዞኑ ውስጥ ለሚገኙት የጤና፣ የትምህርትና የንጹህ መጠጥ ውሃ ተቋማት ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም ለወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ጣቢያው ያለው ፋይዳ እጅግ የጎላ ነው።

ለፕሮጀክቱ መሳካት በቁርጠኝነት ለሠሩት ለክብርት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራሮች፣ ለግንባታ ተቋራጩ የቻይናው ሲኖ ሃይድሮ ኩባንያ እና ለአማካሪው እንዲሁም ለዞኑ የሥራ ኃላፊዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብና አመራር ፕሮጀክቱን ከመጀመሪያው ጀምሮ በባለቤትነት ስሜት ሲደግፉና ሲከታተሉ መቆየታቸውን ያነሱት አቶ ዘይኔ በቀጣይም ይህንን ታላቅ ሀገራዊ መሰረተ ልማት በአግባቡ በመንከባከብና በመጠበቅ ረገድ የበኩሉን ኃላፊነት እንደሚወጣ እምነታቸውን ገልፀዋል።

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/
📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/
📌ድረ- ገፅ https://www.eep.com.et
ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም

"ጣቢያው የአንድ ትውልድ ጥያቄን የመለሰ ነው" ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል..///...የወራቤ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያን መገንባቱ የአንድ ትውልድ ዘመን ጥያቄን መመለስ መቻሉን...
22/05/2026

"ጣቢያው የአንድ ትውልድ ጥያቄን የመለሰ ነው" ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል..///...
የወራቤ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያን መገንባቱ የአንድ ትውልድ ዘመን ጥያቄን መመለስ መቻሉን የኢፌዲሪ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ገለፁ።

ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በማከፋፈያ ጣቢያው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር የኤሌክትሪክ አቅርቦቱ የስልጤ ዞንን ቀጣይ የብልፅግና ጉዞ የሚያፋጥንና የአካባቢውን እምቅ አቅም ወደ ላቀ ምዕራፍ የሚያሸጋግር መሆኑን ገልፀዋል።

የኃይል መሰረተ ልማቱ የአካባቢውን ማህበረሰብ የልማት ፍላጎት ከማርካት ባለፈ የወራቤ ከተማንና አጠቃላይ የስልጤ ዞንን የንግድና የኢኮኖሚ መናኸሪያ ለማድረግ ለተያዘው ግብ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም ነው የተናገሩት።

የወራቤ ከተማ በንግድና በማህበራዊ ትስስር ረገድ ያላትን ስልታዊ ጠቀሜታ ያነሱት ወ/ሮ ሙፈሪያት ከተማዋ በርካታ መጋቢ መንገዶች የሚገናኙባትና ሰፊ የንግድ እንቅስቃሴ የሚስተናገድባት በመሆኗ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ማግኘቷ ስትራቴጂካዊ አቅሟን ይበልጥ እንደሚያጎለብተው ጠቅሰዋል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ በሀገር ደረጃ የተከናወኑ የኤሌክትሪክ ኃይል መሰረተ ልማቶች የሀገሪቱን ከፍታ ያበሰሩ ብቻም ሳይሆኑ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ የኃይል ሚዛንን ያስተካከሉ ትልልቅ ስኬቶች መሆናቸውንም ነው የጠቀሱት።

እንደ ሚኒስትሯ ገለፃ ጣቢያው የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ብቻ ሳይሆን የአካባቢውን ማህበረሰብ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክርና የሚያቀናጅ ታሪካዊ መሰረት ነው።

በአሁኑ ወቅት የኃይል አቅርቦቱ አስተማማኝ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በስልጤ ዞን በግሉ ዘርፍና በመንግሥት ትብብር ወደ አንድ ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የተጀመሩ የኢንዱስትሪ ልማቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ለፕሮጀክቱ ስኬት በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀን ከሌሊት በቁርጠኝነት የሠሩትን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር፣ የሥራ ተቋራጭና አማካሪ አካላትን ያደነቁት ሚኒስትሯ የአካባቢው አመራርና ማህበረሰብም ፕሮጀክቱን በባለቤትነት ስሜት በመንከባከብ ላሳዩት ቀና ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ይህ የተቀናጀ የሥራ ባህልና የባለቤትነት መንፈስ ለሌሎች መሰል ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችም በምሳሌነት ሊወሰድ የሚገባው ታላቅ ተሞክሮ መሆኑንም ነው ያብራሩት።

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/
📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/
📌ድረ- ገፅ https://www.eep.com.et
ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም

"የኤሌክትሪክ ኃይል የብልፅግና ምሰሶ ነው" ኢንጂነር አሸብር ባልቻ..///...የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የሀገሪቱ የብልፅግና ጉዞ ዋነኛ ምሰሶ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ...
22/05/2026

"የኤሌክትሪክ ኃይል የብልፅግና ምሰሶ ነው" ኢንጂነር አሸብር ባልቻ..///...
የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የሀገሪቱ የብልፅግና ጉዞ ዋነኛ ምሰሶ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ገለፁ።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው ኢንጂነር አሸብር ባልቻ የወራቤ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት የጣቢያው መገንባት ተቋሙ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል በመላ ሀገሪቱ ለማዳረስ ለያዘው ስትራቴጂካዊ ግብ ስኬት ትልቅ ማሳያ ነው።

የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ለአገልግሎት መብቃት ለአካባቢው ቀጣይ የዕድገትና የብልፅግና ጉዞ ትልቅ መደላደል እንደሚፈጥርም ነው የተናገሩት።

የጣቢያው ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በይፋ ለማብሰር የተዘጋጀው የምርቃት መርሃ ግብር የተገኘውን ስኬትና ደስታ ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ ለመካፈል መሆኑን አስረድተዋል።

ተቋሙ በመላ ሀገሪቱ በርካታ የኃይል ማመንጫ፣ ማስተላለፊያና የማከፋፈያ ጣቢያዎችን እየገነባ እንደሚገኝ የገለፁት ኢንጂነር አሸብር ዘንድሮ በርካታ ሜጋ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ማብቃቱን አብራርተዋል።

እነዚህ ግዙፍ የኃይል መሠረተ ልማቶች ተመርቀው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ የኃይል አቅርቦት አቅም በከፍተኛ ደረጃ ማደጉንም ነው የገለፁት።

የወራቤ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ የስልጤ ዞንና የወራቤ ከተማ አመራሮች እንዲሁም ማህበረሰቡ ላደረጉት ልዩና አርአያነት ያለው ድጋፍ በተቋሙ ስም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚልን ጨምሮ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/
📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/
📌ድረ- ገፅ https://www.eep.com.et
ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም

Address

Kotebe, Ethiopian Electric Power HQ, Infront Of Kotebe Metal Tools Factory
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 02:00 - 17:00
Wednesday 02:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 02:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Electric Power-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian Electric Power-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል:

Share