Tan Engineering

Tan Engineering Tan Engineering/Sports construction company in Ethiopia. Quality is our difference.

27/05/2026

በሶማሌ ክልል ሰርተን በማጠናቀቅ ላይ የምንገኘው ስታዲየም!

የሃላባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በማደጋችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እንወዳለን። ይህ ስኬት በአጋጣሚ የተገኘ ሳይሆን ለአመታት ተደክሞበት እንደሆነ መመስከር ይ...
15/04/2026

የሃላባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በማደጋችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እንወዳለን።

ይህ ስኬት በአጋጣሚ የተገኘ ሳይሆን ለአመታት ተደክሞበት እንደሆነ መመስከር ይቻላል። በቀጣይም በውቡ ስታዲየማችሁ በደማቅ ደጋፊዎቻችሁ ፊት ስትመኙት የነበረውን የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታን ለማድረግ ያብቃችሁ።

ጠንካራ፣ ስራ ወዳድ እና በልማት ቁርጠኛ የሆነ ማህበረሰብ እና አመራር ከጀርባችሁ ስላለ በፕሪሚየር ሊጉም ስኬታማ እንደምትሆኑ እምነታችን ነው።

በድጋሜ እንኳን ደስ ያላችሁ!
Tan Engineering

04/02/2026
ምቹ የእግር ኳስ መጫዎቻዎችን ማስፋፋት አላማ አድርጎ እየሰራ ያለው ታን ኢንጂነሪንግ በልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን የወረዳ 8 ስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ ግንባታ በይፋ አስጀመረ።  በማስጀመሪያ...
04/02/2026

ምቹ የእግር ኳስ መጫዎቻዎችን ማስፋፋት አላማ አድርጎ እየሰራ ያለው ታን ኢንጂነሪንግ በልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን የወረዳ 8 ስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ ግንባታ በይፋ አስጀመረ።

በማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ: "መንግስት ከለውጡ በኋላ አገር ተረካቢ ትውልድ ለማነፅ የሚያስችሉ የስብዕና መገንቢያ ማዕከላትን እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በመስራት ላይ ይገኛል።

አሁን በልደታ ክፍለ ከተማ የሚገነባው ሜዳም ሳቢ፣ ማራኪና ጥራቱን የጠበቀ ሲሆን፤ ለሌሎች አካባቢዎችም እንደ ሞዴል የሚያገለግል መሆኑን አቶ በላይ ገልፀዋል።

ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው "የስፖርት ማዘውተሪያዎችን ማስፋፋት ወጣቶችን ንቁ፣ ጤናማና ግብረ-ገብነትን የተላበሱ ለማድረግ ያስችላል። ንቁና ብቁ ትውልድ የማፍራት ኃላፊነት የሁላችንም ድርሻ በመሆኑ፣ ይህ ፕሮጀክት ለነገ አገር ተረካቢዎች ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።"

አቶ ክብረዓለም ደምሴ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ም/ቢሮ ሀላፊ: "በርካታ የስፖርት ማዘውተሪያዎችን በጥራትና በአጭር ጊዜ ገንብተን እያስመረቅን እንገኛለን። ይህንም ሜዳ በተቀመጠለት ጊዜ ተጠናቆ ለስፖርት ቤተሰቡ ክፍት እንደሚደረግ ተናግረዋል ።"

የፕሮጀክቱ ስራ ተቋራጭ አቶ ፋአድ ይብራሂም በበኩላቸው፣ የተሰጣቸውን እድል በመጠቀም ስፖርቱ የተሰጠውን ትኩረት በሚመጥን መልኩ ስራውን በጥራትና በጊዜው አጠናቀው እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከልደታ ወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት ከታን ኢንጂነሪግ ጋር በመተባበር በወረዳ 08 ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከል የሚለማው ስፖርት ማዘውተርያ ስፍራ ግንባታው በ3 ወራት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተመልክቷል፡፡

ጥራት፣ ፍጥነት እና ታመመኝነት የማንደራደርባቸው መርሆዎቻችን ናቸው።  አደራችንን ለመወጣት እና ደንበኞቻችን በስራችን እንዲኮሩ ብሎም እንዲመሰክሩ ማድረግ የዘወትር ትጋታችን ነው። Tan En...
11/01/2026

ጥራት፣ ፍጥነት እና ታመመኝነት የማንደራደርባቸው መርሆዎቻችን ናቸው። አደራችንን ለመወጣት እና ደንበኞቻችን በስራችን እንዲኮሩ ብሎም እንዲመሰክሩ ማድረግ የዘወትር ትጋታችን ነው።

Tan Engineering

11/01/2026

ውድ ሃላባዎች እንኳን ለዘመን መለወጫ 'ሴራ' በዓል አደረሳችሁ! እኛም በዚህ ቀን የሰጣችሁንን አደራ በከፍተኛ ጥራት ተወጥተን በማስረከባችን ድርብ ደስታ ተሰምቶናል።

የሃላባ ስታዲየም የትራክ ንጣፍ ስራ በስኬት ተጠናቋል!
04/01/2026

የሃላባ ስታዲየም የትራክ ንጣፍ ስራ በስኬት ተጠናቋል!

27/10/2025

Credit: Dire tv

Address

Semay Tower
Addis Ababa
ADDIS

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tan Engineering posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share