Ethiopia Today

Ethiopia Today A global news provider! Engineers | Architects I Interior Designers I Builders I 3D Visualizers!
(2)

የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT Exam) የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ***//***ሐምሌ 18/2018 ዓ/ም የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በ2018 ዓ.ም የሚሰጠውን መደበኛ የድህ...
25/07/2026

የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT Exam) የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ
***//***
ሐምሌ 18/2018 ዓ/ም

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በ2018 ዓ.ም የሚሰጠውን መደበኛ የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና /National Graduate Admission Test/ ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ፈተናውን ለመውሰድ እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ የድህረ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች በሙሉ ምዝገባ የሚካሄደው ከሀምሌ 15 – 25/2018 ዓ.ም ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ከታች በተቀመጠው የመመዝገቢያ ሊንክ ገብታችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ለፈተናውም አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን። የፈተና መስጫ ጊዜው ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል፡፡

የመመዝገቢያ ሊንክ፡- https://ngat.ethernet.edu.et

ማሳሰቢያ:-
ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ እንደ ቅድመ ሁኔታ መቀመጡን አውቃችሁ ከወዲሁ እንድትዘጋጁ።

የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር (ሰባት መቶ ሀምሳ ብር) መሆኑን አውቃችሁ በቴሌ ብር በኩል በምዝገባው ወቅት የሚፈጸም ይሆናል።
ምዝገባው የሚከናወነው በሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ሲሆን የፈተና ጣቢያውን በሚመለከት ግን ከምዝገባ በኋላ የተመዝጋቢ ቁጥሩ ታይቶ በስታንዳርዱ መሰረት የሚወሰን ይሆናል፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

«መንግሥት የሕዝቡን የኑሮ እውነታ በቁጥር ጨዋታ ከመሸፈን ይውጣ» ‎‎ዶክተር ደሣለኝ ጫኔ‎‎  | ​ባለፉት አምስት ዓመታት የሕዝቡን የኑሮ ስቃይና የመንግሥትን መዋቅራዊ ድክመቶች በቅርበት ሲ...
07/07/2026

«መንግሥት የሕዝቡን የኑሮ እውነታ በቁጥር ጨዋታ ከመሸፈን ይውጣ»

‎ዶክተር ደሣለኝ ጫኔ

‎ | ​ባለፉት አምስት ዓመታት የሕዝቡን የኑሮ ስቃይና የመንግሥትን መዋቅራዊ ድክመቶች በቅርበት ሲታዘቡ መቆየታቸውን የገለጹት የፓርላማ አባል ዶክተር ደሣለኝ ጫኔ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መንግሥት ላይ ጠንከር ያሉ የትችትና የጥያቄ ጠይቀዋል።

‎ስድስተኛው የፓርላማ ዘመን አምስተኛ ዓመት ማጠቃለያ የመንግሥት ሪፖርት በቀረበበት ወቅት ንግግር ያደረጉት የሕዝብ ተወካዩ፣ መንግሥት በተለያዩ አካባቢዎች የቀጠሉትን የሰላም እጦቶችና የፖለቲካ ምኅዳሩን መጥበብ ችላ በማለት፣ በኢኮኖሚ ስኬት ስም የቁጥር ጨዋታዎችን እያቀረበ ሕዝብን እያደናገረ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

‎በተለይም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የመጣው ሰማይ የነካ የዋጋ ግሽበት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን የመግዛት አቅም ያሳጣና መካከለኛውን የኅብረተሰብ መደብ ያጠፋ ስውር ረሃብ መውለዱን ገልጸዋል።

‎​በትምህርት ዘርፍ በኩል የታየውን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የ92 በመቶ መውደቅ ሲሉ የገለጹት ዶክተር ደሣለኝ፣ ይህ አሳሳቢ ውጤት የመንግሥትን የትምህርት ሥርዓት መዋቅራዊ ኪሳራ የሚያሳይ በመሆኑ ትምህርት ሚኒስትሩ ሊጠየቁበት ይገባል ብለዋል።

‎አያይዘውም በሀገሪቱ ሰብአዊ ቀውስ እያለ የመረጃ ማጥራት በሚል ሰበብ የእርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ወደ 2.3 ሚሊዮን ዝቅ ተደርጎ መቅረቡ እውነታውን የማይወክል የፖለቲካ ቁጥር ማሳመሪያ ነው ሲሉ ነቅፈዋል።

‎ተወካዩ እንደ መፍትሔ ያቀረቡት መንግሥት ትኩረቱን ከኮሪደር ልማትና ከሪዞርቶች ግንባታ በመቀነስ፣ ወደ መሠረታዊ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ ወደ ማኅበራዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራሞችና ሁሉንም የታጠቁ ኃይሎች ያካተተ እውነተኛ ብሔራዊ የፖለቲካ ድርድር ላይ እንዲያደርግ ነው።

‎በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ችግሮችን በኃይል ከመፍታት ወጥተው፣ ሕዝቡ በአዲሱ የ2019 ዓመተ ምህረት በተግባር ሊያየው የሚችለውን ግልጽ የሰላም የጊዜ ሰሌዳና ቁርጠኝነት እንዲያብራሩ በይፋ ጠይቀዋል።

የስራ ማስታወቂያበኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኮንስትራክሽን ልማት ቢዝነስ ዘርፍ ከዚህ በታች ለተገለጹ የስራ መደቦች መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ ...
30/06/2026

የስራ ማስታወቂያ
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኮንስትራክሽን ልማት ቢዝነስ ዘርፍ ከዚህ በታች ለተገለጹ የስራ መደቦች መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

1. የስራ መደቡ መጠሪያ፤ የፕሮጀክት ክትትል ስራ አስኪያጅ
ደረጃ፣15
ብዛት፤01
ተፈላጊ የትምህርት አይነት፤ በሲቭል ምህንድስና፣ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ወይም ተዛማጅ
የትምህርት ደረጃ፤ ማስተርስ/ባችለር ዲግሪ
የስራ ልምድ ፤ 6/8 ዓመት
የቅጥር ሁኔታ ፤ ቋሚ
የስራ ቦታ ፤ አዲስ አበባ
2. የስራ መደቡ መጠሪያ፤ የፕሮጀክት ዋጋ ቁጥጥር ስራ አስኪያጅ
ደረጃ፣15
ብዛት፤01
ተፈላጊ የትምህርት አይነት፤ በሲቭል ምህንድስና፣ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ወይም ተዛማጅ
የትምህርት ደረጃ፤ ማስተርስ/ባችለር ዲግሪ
የስራ ልምድ ፤ 6/8 ዓመት
የቅጥር ሁኔታ ፤ ቋሚ
የስራ ቦታ ፤ አዲስ አበባ

3. የስራ መደቡ መጠሪያ፤ ከፍተኛ የኮንትራት አስተዳደር ባለሙያ
ደረጃ፣14
ብዛት፤01
ተፈላጊ የትምህርት አይነት፤ በሲቭል ምህንድስና ወይም ተዛማጅ
የትምህርት ደረጃ፤ ማስተርስ/ባችለር ዲግሪ
የስራ ልምድ ፤ 4/6 ዓመት
የቅጥር ሁኔታ ፤ ቋሚ
የስራ ቦታ ፤ አዲስ አበባ
4. የስራ መደቡ መጠሪያ፤ የኮንትራት አስተዳደር ባለሙያ
ደረጃ፣13
ብዛት፤01
ተፈላጊ የትምህርት አይነት፤ በሲቭል ምህንድስና ወይም ተዛማጅ
የትምህርት ደረጃ፤ ማስተርስ/ባችለር ዲግሪ
የስራ ልምድ ፤ 2/4 ዓመት
የቅጥር ሁኔታ ፤ ቋሚ
የስራ ቦታ ፤ አዲስ አበባ
5. የስራ መደቡ መጠሪያ፤ ከፍተኛ የቢሮ መሀንዲስ
ደረጃ፣14
ብዛት፤01
ተፈላጊ የትምህርት አይነት፤ በሲቭል ምህንድስና፣ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ወይም ተዛማጅ
የትምህርት ደረጃ፤ ማስተርስ/ባችለር ዲግሪ
የስራ ልምድ ፤ 4/6 ዓመት
የቅጥር ሁኔታ ፤ ቋሚ
የስራ ቦታ ፤ አዲስ አበባ
6. የስራ መደቡ መጠሪያ፤ የቢሮ መሀንዲስ
ደረጃ፣13
ብዛት፤01
ተፈላጊ የትምህርት አይነት፤ በሲቭል ምህንድስና፣ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ወይም ተዛማጅ
የትምህርት ደረጃ፤ ማስተርስ/ባችለር ዲግሪ
የስራ ልምድ ፤ 2/4 ዓመት
የቅጥር ሁኔታ ፤ ቋሚ
የስራ ቦታ ፤ አዲስ አበባ

7. የስራ መደቡ መጠሪያ፤ ከፍተኛ ኤሌክትሪካል ባለሙያ
ደረጃ፣14
ብዛት፤01
ተፈላጊ የትምህርት አይነት፤ በኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ፣ፓወር ሲስተም ኢንጅነሪንግ ወይም ተዛማጅ
የትምህርት ደረጃ፤ ማስተርስ/ባችለር ዲግሪ
የስራ ልምድ ፤ 4/6 ዓመት
የቅጥር ሁኔታ ፤ ቋሚ
የስራ ቦታ ፤ አዲስ አበባ

8. የስራ መደቡ መጠሪያ፤ ከፍተኛ ሴፍቲ ኢንጅነር
ደረጃ፣14
ብዛት፤01
ተፈላጊ የትምህርት አይነት፤ በሲቭል ኢንጅነሪንግ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት እና ተዛማጅ
የትምህርት ደረጃ፤ ማስተርስ/ባችለር ዲግሪ
የስራ ልምድ ፤ 4/6 ዓመት
የቅጥር ሁኔታ ፤ ቋሚ
የስራ ቦታ ፤ አዲስ አበባ

9. የስራ መደቡ መጠሪያ፤ ከፍተኛ ሲቭል መሀንዲስ
ደረጃ፣14
ብዛት፤01
ተፈላጊ የትምህርት አይነት፤ በሲቭል ምህንድስና፣ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ወይም ተዛማጅ
የትምህርት ደረጃ፤ ማስተርስ/ባችለር ዲግሪ
የስራ ልምድ ፤ 4/6 ዓመት
የቅጥር ሁኔታ ፤ ቋሚ
የስራ ቦታ ፤ አዲስ አበባ

10. የስራ መደቡ መጠሪያ፤ ሲቭል መሀንዲስ
ደረጃ፣13
ብዛት፤01
ተፈላጊ የትምህርት አይነት፤ በሲቭል ምህንድስና፣ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ወይም ተዛማጅ
የትምህርት ደረጃ፤ ማስተርስ/ባችለር ዲግሪ
የስራ ልምድ ፤ 2/4 ዓመት
የቅጥር ሁኔታ ፤ ቋሚ
የስራ ቦታ ፤ አዲስ አበባ

11. የስራ መደቡ መጠሪያ፤ ከፍተኛ ሰርቬይንግ ባለሙያ
ደረጃ፣14
ብዛት፤01
ተፈላጊ የትምህርት አይነት፤ በሰርቬይንግ፣ ሲቭል ምህንድስና፣ በሰርቬይንግ ደረጃ 4 እና በላይ
የትምህርት ደረጃ፤ ማስተርስ/ባችለር ዲግሪ/ደረጃ 4/5
የስራ ልምድ ፤ 4/6/8 ዓመት
የቅጥር ሁኔታ ፤ ቋሚ
የስራ ቦታ ፤ አዲስ አበባ

12. የስራ መደቡ መጠሪያ፤ ከፍተኛ አርኪቴክት
ደረጃ፣14
ብዛት፤01
ተፈላጊ የትምህርት አይነት፤ በአርክቴክቸር ወይም ተዛማጅ
የትምህርት ደረጃ፤ ማስተርስ/ባችለር ዲግሪ
የስራ ልምድ ፤ 4/6 ዓመት
የቅጥር ሁኔታ ፤ ቋሚ
የስራ ቦታ ፤ አዲስ አበባ

13. የስራ መደቡ መጠሪያ፤ ኳንቲቲ ሰርቬየር
ደረጃ፣13
ብዛት፤01
ተፈላጊ የትምህርት አይነት፤ በሰርቬይንግ፣ ሲቭል ምህንድስና፣ በሰርቬይንግ ደረጃ 4 እና በላይ
የትምህርት ደረጃ፤ ማስተርስ/ባችለር ዲግሪ/ደረጃ 4/5
የስራ ልምድ ፤ 2/4/6 ዓመት
የቅጥር ሁኔታ ፤ ቋሚ
የስራ ቦታ ፤ አዲስ አበባ

14. የስራ መደቡ መጠሪያ፤ ከፍተኛ የግዥ ባለሙያ
ደረጃ፣14
ብዛት፤01
ተፈላጊ የትምህርት አይነት፤ በፕሮኪዩርመንት ወይም በሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት
የትምህርት ደረጃ፤ ማስተርስ/ባችለር ዲግሪ
የስራ ልምድ ፤ 4/6 ዓመት
የቅጥር ሁኔታ ፤ ቋሚ
የስራ ቦታ ፤ አዲስ አበባ

ማሳሰቢያ፣
• የምዝገባ ሁኔታ፡ በኦን ላይን፡- https://tinyurl.com/IPDC-CDB-Vacancy6
• ለሥራ መደቡ የሚያስፈልጉ የትምህርት ፤ሥራ ልምድ እና ሌሎች ማስረጃዎች ወደ ፒዲኤፍ/pdf በመቀየር በአንድ ፋይል ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
• በስራ መደቡ ላይ የልዩ ብቃት ማስረጃ ማቅረብ ዋጋ ያሰጣል
• ደመወዝ ፡- በኮርፖሬሽኑ ደመወዝ ስኬል መሰረት
• የምዝገባ ቀን ፡ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ፡፡
• አመልካቾች ከስራ መደቡ ጋር ቀጥተኛ የሆነ የስራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
• ከግል ድርጅቶች የሚቀርብ ስራ ልምድ ግብር መከፈሉ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ስልክ ቁጥር 011 658 22 11
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን
የኮንስትራክሽን ልማት ቢዝነስ ዘርፍ

ማን አሸንፎ ዋንጫ ያነሳል? 🏆🇫🇷 Paris Saint Germain Vs Arsenal 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 ⏰ 1:00 🏟️ Puskash Arena, Hungary 🇭🇺
30/05/2026

ማን አሸንፎ ዋንጫ ያነሳል? 🏆
🇫🇷 Paris Saint Germain Vs Arsenal 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿
⏰ 1:00
🏟️ Puskash Arena, Hungary 🇭🇺

ታላቅ የትምህርት ዕድል !የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበርየኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ጠንካራ ሀገራዊ የኒውክሊየር መሰረተ ልማት ለመገንባት የሚ...
29/05/2026

ታላቅ የትምህርት ዕድል !

የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር

የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ጠንካራ ሀገራዊ የኒውክሊየር መሰረተ ልማት ለመገንባት የሚያስፈልገውን በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ የኒውክሊየር ባለሙያዎችን ለማፍራት ከሚያከናውናቸው ቁልፍ ተግባራት መካከል አንዱ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችና ሰልጣኞችን ወደ ውጭ ሀገራት በመላከ በዘርፉ ትምህርትና ስልጠና እንዲያገኙ ማስቻል ነው። በዚሁ መሰረት ኮሚሽኑ እ.ኤ.አ 2026/27 የትምህርት ዘመን ፍላጎት ያላቸውን ኢትዮጵያዊያን አመልካቾችን አወዳድሮ በሩሲያ በሚገኙ ስመጥር የሳይንስና የምህንድስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ከዚህ በታች በሰፈሩት የትምህርት ዓይነቶች እና የመወዳደሪያ መሥፈርቶች የሚያሟሉ ብቁ አመልካቾችን ለምዝገባ ይጋብዛል፡፡

የስልጠናና ትምህርት ዘርፎች፡-
• Nuclear Power Engineering and Heat Physics (BSc)
• Nuclear Physics and Technology (BSc)
• Nuclear Power Plants Design, Operation and Engineering (BSc)
• Heat Power Engineering (BSc)
• Nuclear Power Engineering and Heat Physics (MSc)
• Management/ Management in Technological Systems (MA)

የመወዳደሪያ መሥፈርቶች ፡-
• ለመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች እድሜያቸው ከ 20 ዓመት ያልበለጠ እና የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ አማካኝ ውጤት ከ 500 በላይ ያመጣች ወይም ያመጣ፣
• ለሁለተኛ ዲግሪ አመልካቾች እድሜያቸው ከ 30 ዓመት ያልበለጠ በሳይንስና ምህንድስና ዘርፍ በከፍተኛ ውጤት የተመረቀች ወይም የተመረቀ፣
• ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፡፡

በመሆኑም ኮሚሽኑ ያወጣውን የምዝገባ ቅድመ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 ቀናት የትምህርት ውጤት ማስረጃ እና ሌሎች ደጋፊ ሰነዶች ኮፒ አባሪ በማድረግ ከታች በሰፈረው የኮሚሽኑ የኢሜል አድራሻ የኤሌክትሮኒክ ኮፒ እንድትልኩ እናሳውቃለን፡፡

Email: [email protected]
መልካም ዕድል!

"ከጃኒ ጋር ያለን የፍቅር ግኑኝነት አብቅትዋል ይገባኛል በምን ምክንያት እዚህ ደረጃ እንደደረስን ማወቅ እንደምትፈልጉ ምንም ያህል ብወዳቹም ግን ኣንድ ኣንድ ነገሮች ለራሴ ማስቀረትን መርጫለ...
28/05/2026

"ከጃኒ ጋር ያለን የፍቅር ግኑኝነት አብቅትዋል ይገባኛል በምን ምክንያት እዚህ ደረጃ እንደደረስን ማወቅ እንደምትፈልጉ ምንም ያህል ብወዳቹም ግን ኣንድ ኣንድ ነገሮች ለራሴ ማስቀረትን መርጫለሁ ህይወት ነውና ያጋጥማል አከብራቹሃለሁ።" አዶናይ

የጥንቃቄ = መልዕክት  ዛሬ ግንቦት 06/09/2018ዓ/ም በዕለተ ሀሙስ ከቀኑ 8:00 ሰዓት በግምት በምሆንበት ጊዜ ስሙ ሁሴን ወዕሌቦ ሁሎሮ አድራሻው ከንባታ ዞን አድሎ ዙርያ ወረደ ሸሸራ ...
14/05/2026

የጥንቃቄ = መልዕክት

ዛሬ ግንቦት 06/09/2018ዓ/ም በዕለተ ሀሙስ ከቀኑ 8:00 ሰዓት በግምት በምሆንበት ጊዜ ስሙ ሁሴን ወዕሌቦ ሁሎሮ አድራሻው ከንባታ ዞን አድሎ ዙርያ ወረደ ሸሸራ ቸፌ ቀበሌ ነዋሪ የሆነውን ግለሰብ አንድ አርሶ አደር ግለሰብ ስሙ አቶ አበራ የምባል አድራሻው ሀ/ቁ/ከ/በሜጦ ቀበሌ በጋለቶ ቀጠና ነዋሪ ሲሆን ግለሰቡ በሜጦማ ቀበሌ በዋንጃ ዋልድያ በቡሼ ንዑስ መንደር ውስጥ የዘረውን ቦቆሎ ለማስኮተኮት

ከዝህ በላይ በስም የተጠቀሰውን ሟች ሁሴን ወዕሌቦ ሁሎሮ የተባለውን ግለሰብ ቦቆሎውን እንድኮተክትለት በገንዘብ 700ብር ተስማምቶ
ለስራ ያስገባዋል። ይህ ግለሰብ ስራውን የጀመረው ከረፋዱ 4:00 ሰዓት አከባቢ ስሆን ለዝህ ግለሰብ/ሟች/የአቶ አበራ ባለቤት ወደ በቆሎ ማሳ ምሳና ውሃ ይዛለት ትሄዳሌች

ምሳውን ሴትዮዋ ስትወስድለት ሟቹ በኩትኳቶ ስራው ላይ እንደነበር ትናገራሌች ከዝያ ሴትዮዋ ሰራተኛውን ወደ ጥላ ሆነህ ምሳህን ብላ ትለዋሌች ከዝያ ሟቹም እሽ ይልና እዝህ ጋ አምጭልኝ ብሎ በቆርቆሮ ወደታጠረው አጥር ጥግ ሄዶ ቁጭ እንዳላ ምሳውንም ሳይበላ የመጨረሻ ምሳውን የወሰደችለት ሴትዮዋ ምግቡንም ከዛንብሏም ሳታወጣ እዛቹ ተደግፎ የተቀመጠውን የቆርቆሮ አጥሩን እንደተደገፋም በዛችው ቅጽበት ምግቡንም ሳይበላ ህይወቱ ልያልፍ እንደቻላ ትናገራሌች

በወቅቱም የሟችን ሁኔታ የተመለከተችው ሴትዮ ሌሎች ሰዎችን ጠርታ ስለሟቹ አሟሟት ሁኔታ ታስረዳሌች ከዝያ በመቀጠል ለፖሊስ ይደዎላል በፍጥነት የደረሰው ፓሊስም የሟቹን ማንነትና አድራሻ ለማወቅ በአስክሬኑ ላይ መታወቂያ ይፈልግና ልያገኝ አልቻለም ከዝያም ሟቹን ከሰራተኛ ተራ አምጥቶ የቀጠረውን ግለሰብ/አቶ አበራ የተባለውን አስጠርቶ

ይህን ግለሰብ/ሟች/ስሙንና አድራሻውን ጠይቄህ ነበር ወይ? ስል ፓሊስ ይጠይቀዋል ስጠይቀው ስሙን አልጠየኩም አድራሻውን ስጠይቀው አድሎ ዙሪያ ወረዳ ከሸሸራቸፌ እንደመጣ ነግሮኛል መታወቂያ ግን አልጠየኩትም ስል ለፖሊስ ይናገራል።

ከዝያ ሪፖርት የተደረገለት የቁሊቶ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ረ/ኢ/ር ሹክራላ ሸ/ሱጋቶ የወንጀል መከላል ፓ/አባላትንና ፓትሮል መኪና ይልካል አስክሬኑ በዝህ መኪና ተጭኖ ምናልባት የምያውቀው ሰው ከተገኘ በምል ወደ ሰራተኛ ተራ ተወስዶ የምያውቀው ሰው ከተገኘ ተብሎ ስጠያያቅ የሟችን ሙሉ ስሙንና አድራሻውን የምያውቅ ሰው ተገኝቷል በዝህ መልኩ ለማወቅ ተችሏል።

ዘመድ የምሆንለትን ሰው በዝህ መልኩ እንድመጣ የተደረጋ ስለሆነ

አሁን ለህብረተሰባችን የምናስተላልፈው ዋናው
መልዕክታችን ማንኛውንም የቀን ሰራተኛ ለስራ ስንፈልግ / ስንቀጥር አስቀድመን ስሙንና ሙሉ አድራሻውን በትክክል የምገልጽ ብቻል የድጅታል መታወቂያ ካልሆነም ብያንስ የቀበሌ መታወቂያ መያዙን ያረጋግጡ።

ሉዊስ ኤንሪኬ፡- “በመልስ ጨዋታ የተለየ ጨዋታ አልጠብቅም። የተቻልንን እንሞክራለን።” 🔥
29/04/2026

ሉዊስ ኤንሪኬ፡- “በመልስ ጨዋታ የተለየ ጨዋታ አልጠብቅም። የተቻልንን እንሞክራለን።” 🔥

የትራንስፖርት ታሪፍ በተወሰነው መሰረት እንዲቀጥል ትዕዛዝ ተላለፈየትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የትራንስፖርት ታሪፍ በተወሰነው መሰረት ብቻ እንዲቀጥል ተዕዛዝ አስተላልፏል።ሚኒስቴሩ ...
29/04/2026

የትራንስፖርት ታሪፍ በተወሰነው መሰረት እንዲቀጥል ትዕዛዝ ተላለፈ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የትራንስፖርት ታሪፍ በተወሰነው መሰረት ብቻ እንዲቀጥል ተዕዛዝ አስተላልፏል።

ሚኒስቴሩ የትራንስፖርት አገልግሎት ወደ መደበኛ ሁኔታ መመለሱን ለማሳወቅ ባወጣው መግለጫ÷ በመካከለኛው ምሥራቅ የተከሰተው ግጭት በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሮ የነዳጅ ዋጋ ግሽበትና በአቅርቦት ላይ መስተጓጎል እንዲፈጠር አድርጓል ብሏል።

ይህም ሁኔታ በኢትዮጵያ የናፍታ ዕለታዊ አቅርቦትን ከ9 ሚሊየን ሊትር ወደ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር እንዲቀንስ አድርጎ በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የሚታወቁ መስተጓጎሎችን አስከትሎ እንደነበር አስታውሷል።

መንግሥት ይህንን ችግር በፍጥነት ለመቆጣጠር የታሪፍ ማሻሻያ፣ የአቅርቦት አደረጃጀት ማሻሻል እና የሎጂስቲክስ ቅንጅት ማጠናከርን ጨምሮ በርካታ አስቸኳይ እና ዘላቂ ርምጃዎች መውሰዱን አመልክቷል።

ይህም የውጭ ጫናዎች ቢኖሩም የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ መረጋጋትን በመጠበቅ እና የሕዝብ አገልግሎቶች እንዳይቋረጡ በማድረግ በኩል መንግሥት የሕዝብ ጥቅምን በማስቀደም የሚከተለውን የፖሊሲ አቅጣጫ የሚያሳይ መሆኑን አስረድቷል።

ዛሬ የገንዘብ ሚኒስቴር በይፋ እንዳሳወቀው የነዳጅ አቅርቦት ወደ መደበኛ ሁኔታው ተመልሷል ያለው ሚኒስቴሩ÷ ይህ ሁኔታ በትራንስፖርት ዘርፍ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች በፍጥነት እንዲፈቱ ያስችላልም ብሏል።

በመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ ቀደም ሲል በነዳጅ እጥረት ምክንያት የተፈጠሩ የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጎሎች ሙሉ በሙሉ እንዲቀረፉ፣ ከአዲስ አበባ እስከ ክልሎች የሚገኙ ሁሉም የዘርፉ አመራሮች እና ተዋናዮች ታሪፍ በተወሰነው መሰረት ብቻ እንዲቀጥል በጥብቅ እንድከታተሉና ትግበራውንም በጋራ ግብረ ኃይል እንዲያረጋግጡ አሳስቧል፡፡

መንግሥት የሕዝብ ኑሮ መረጋጋትን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ቀጣይነትን መጠበቅ እና የትራንስፖርት አገልግሎት በዘላቂ መልኩ እንዲጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት ይቀጥላል ሲልም አስገንዝቧል።

በ'ፊንቴክ ኢንቨስትመንት' የማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች ላይ አቃቢ ህግ ክስ መስርቶ እንዲያቀርብ ሰባት ቀናት ተፈቀደለት። የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፥ ...
29/04/2026

በ'ፊንቴክ ኢንቨስትመንት' የማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች ላይ አቃቢ ህግ ክስ መስርቶ እንዲያቀርብ ሰባት ቀናት ተፈቀደለት።

የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፥ በ'ፊንቴክ ኢንቨስትመንት' የማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች ላይ መርማሪ ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ እንዲያቀርብ ለዛሬ ሚያዚያ21/2018 ዓም ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።

በቀጠሮው መሰረት የተሰየመው ችሎቱ ሚያዝያ 9/2018 ዓም በተሰየመበት ወቅት መርማሪ ፖሊስ ጠይቆት ከነበረው የተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ውስጥ ችሎቱ "ፖሊስ የመጨረሻ የምርመራ መዝገቡን አደራጅቶ እንዲያቀርብ በሚል" በሰጠው የሰባት ቀናት ጊዜ መሰረት በፖሊስ በኩል የተጠናቀረውን የምርመራ መዝገብ በዛሬው ዕለት አድምጧል።

መርማሪ ፖሊስ በተሰጠው ጊዜ የክስ መዘገቡን አደራጅቶ ለአቃቢ ህግ ማቅረቡን ገልጿል።

በአጠቃላይ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ከ 7 ሺ ገጾች በላይ የክስ መዝገብ መደራጀቱን የገለጸው አቃቢ ህግ በመዝገቡ ላይ 1ሺ 400 ተበዳዮች መኖራቸውን ከእነዚህ ተበዳዮችም ፖሊስ የ150ውን ቃል መቀበሉን ፣ ከ 12 ሚዲያዎች፣ከ 15 ባንኮች ደግሞ በተጠርጣሪዎች ዙሪያ ያሉትን መረጃዎችን መሰብሰቡን በዝርዝር አስረድቷል።

ስለሆነም ያለውን የማስረጃ ብዛት፣ የተበዳዮችን ብዛት፣ እና የጉዳዩን ክብደት ከግምት ውስጥ በማስገባት መዝገቡ ሊያስከትል የሚችለው ተደራራቢ ክስ የመመስረቻ የ 10 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠን ሲል አቃቢ ህግ ችሎቱን ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው "ተጠርጣሪዎቹ ማህበራዊ መሰረት ያላቸው፣ የጤና እክል ያለባቸው እንዲሁም በተፈለጉበት ጊዜ ሊመጡ የሚችሉ መሆናቸውን በመጥቀስ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ተከራክረዋል።

በተጨማሪም የምርመራ መዝገቡ ተጠናቆ ለአቃቢ ህግ መቅረቡን በመግለጽ አቃቢ ህግ ክሱን እስኪመሰርት ደንበኞቻችን በእስር መቆየት የለባቸውም በማለት ለችሎቱ አስረድተዋል።

የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ችሎቱ አቃቢ ህግ ለክስ መመስረቻ ከጠየቀው የ 10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ሰባቱን ቀናት በመፍቀድ ክስ መስርቶ እንዲያቀርብ ለ28/08/18 ዓ/ም ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Address

Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia Today posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share